Consortium of Self Help Group Approach Promoters (CoSAP) is an umbrella of SHG promoting organizations. Members, who adopt the SHG approach as a key tool for the empowerment of women, utilize this platform as a unifying mechanism for the implementation of the approach. This objective is realized through the provision of capacity building training to member organization and representing them in any policy level discussion that paves the ground for the proliferation of the approach.

+251-115-525251
info@shgconsortiumeth.org
Lideta Sub City, Woreda 10, African Union Area
+251-115-525251

እንካን ወደ ወሊንካና ጥምረት ድረ-ገጽ በደህና መጡ፡፡ በዚህ ገጽ ላይ ስለ ወሊንካና ጥምረት፣ ስራዎች እና የተለያዩ ነጥቦችን እናስተዋውቃለን፡፡ ስለ ጥምረቱ የበለጠ ለማወቅ ወይም በአጋርነት ለመስራት ከፈለጉ ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ያግኙን፡፡ መልካም ቆይታ፡፡

ራዕይ- በቢሾፍቱ ከተማ ብሎም በኢትዮጵያ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶችና የማህበረሰብ ክፍሎች ሁለንተናዊ መብቶቻቸውን አውቀው በሰላም፣ ፍትህ ከማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸው ተላቀው ማየት ነው፡፡

ተልዕኮ፡- ሁሉም የራስ አገዝ ቡድኖች ህብረተሰቡን በማጠናከር በማንቀሳቀስ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ህይወታቸውን መለወጥ እና መብቶቻቸው እንዲከበር ማድረግ፡፡

ዓላማ፡- በአጠቃላይ በከተማው ማህበረሰብ ውስጥ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙት እናቶች ያላቸውን ሀብት በማንቀሳቀስ ከኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮቻቸው እንዲላቀቁ በማድረግ ስለ እናቶች እና ስለ ሕፃናት ሰላም፣ ፍትህ፣ እና ነፃነት እንዲያገኙ መስራት፡፡

+የወሊንካና ጥምረት መዋቅር

...

+የወሊንካና ጥምረት ተግባራት

1ኛ. ስራዎችን ከድርጅቱ በመረከብ ጠንካራ የህዝብ ተቋም መመስረት
  • አባል ቡድኖች፣ ህብረቶች በሚገባ እንዲንቀሳቀሱ ማስቻል፣
  • ከቡድን ወደ ህብረት ከዚያም ወደ ጥምረት እንዲሁም በተቃራኒው የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ማመቻቸት፡፡

2ኛ. የህብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ግልጋሎቶችን ማቅረብ

  • መረጃዎችን በማጠናከር ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ፣
  • የማህበረሰብ ኢንሹራንስ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ማመቻቸት፣
  • የተለያዩ የግንዛቤ ፕሮግራሞችን መስራት፣
  • የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን መስራት፣
  • ከመንግስት ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር ህብረተሰቡን ማገልገል፡፡

3ኛ. ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ሰላም፣ መብትና ፍትህ ላይ መስራት

  • ህብረተሰቡ ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲቆጠብና ከአደጋ እንዲጠበቅ ማመቻቸት፣
  • በህፃናት፣ በሴቶች እና በሰው ልጆች መብቶች ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር፡፡

4ኛ. በመንግስት ፖሊሲና በህብረተሰቡ አስተሳሰብ ላይ በጎ ተፅእኖ ማሳደር 

  • የተለያዩ የመንግስት አካላት ህብረተሰቡን ሊጠቅም በሚችል ህጎችና ፖሊሲዎች ላይ መስራት፣
  • የህጻናት፣ የሴቶች ብሎም የሰዎችን መብቶችና ሌሎች ችግሮችን በተመለከተ ድጋፍ ማድረግ፣
  • በኤች.አይ.ቪ ኤድስ፣ በልጆች የጉልበት ብዝበዛ፣ በሴቶችና ህጻናት መብት ጥሰት ጉዳዮች በተመለከተ የተለየ ትግበራን ማከናወን
  • ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን፡፡

+የወሊንካና ጥምረት መገለጫ

በ2014 ዓ.ም በጥምረቱ ስር ያሉ ቡድኖች፣ ህብረቶች እና እንቅስቃሴያቸው የሚከተለውን ይመስላል፤  
  • በጥምረቱ ስር ያሉ የራስ አገዝ ቡድኖች ብዛት፡ 70
  • የህብረቶች ባዛት፡ 6
  • ጠቅላላ የአባላት ብዛት፡ 980
  • የራስ አገዝ ቡድኖች ቁጠባ፡ 1 ሚሊዮን 287 ሺ ብር
  • በብድር የተዘዋወረ፡ ብር  1 ሚሊዮን 29 ሺ ብር

+ወሊንካና ጥምረት ባከናወናቸው ተግባራት የተገኙ ውጤቶች

  • አባል እናቶች የመቆጠብ ባህላቸውን በማዳበር በተቅላላው ብር 1 ሚሊዮን 287 ሺ ብር መቆጠብ ችለዋል፣
  • የህጻናትና ሴቶች መብት ላይ በተሰራው ስራ በማህበረሰቡ ውስጥ የግንዛቤ መሻሻል ታይቷል፣
  • የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የራስ አገዝ ተቋማትን መደገፍ ችለዋል፣
  • የቤተሰብ ጥንካሬ እና የህጻናት መልካም አስተዳደግ ላይ ትኩረት ማግኘት ችሏል፣
  • የእናቶች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም መገንባት ተችሏል
  • የስርዓተ ጾታ ግንዛቤ ማደግ፣ የቤተሰብ ምጣኔ አስተሳሰብ መጎልበት፡፡