Consortium of Self Help Group Approach Promoters (CoSAP) is an umbrella of SHG promoting organizations. Members, who adopt the SHG approach as a key tool for the empowerment of women, utilize this platform as a unifying mechanism for the implementation of the approach. This objective is realized through the provision of capacity building training to member organization and representing them in any policy level discussion that paves the ground for the proliferation of the approach.

+251-115-525251
info@shgconsortiumeth.org
Lideta Sub City, Woreda 10, African Union Area
+251-115-525251

መግቢያ
የራስ አገዝ ጥምረት በራስ አገዝ ቡድን አሰራር መሰረት 3ኛው እና የአሰራሩ መገለጫ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በስራ ላይ ከሚገኙት ጥምረቶች መካከል በአማራ ክልል ደብረማርቆስ ከተማ ላይ እድገት ባንድነት ጥምረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህ የእድገት ባንድነት ጥምረት ድረ ገፅ ስለ ጥምረቱ አመሰራረት እና እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቅ ነው፡፡ ስለ እድገት ባንድነት ጥምረት የበለጠ ለማወቅ ከታች ያሁትን መረጃዎች እንዲያነቡ በክብር እንጋብዛለን፡፡

  አብራችሁን ለመስራት ብትሹ በአድራሻችን እንድታገኙን ይሁን፡፡     

+ ስለ ራስ አገዝ ጥምረት ፅንሰ ሀሳብ

በራስ አገዝ ቡድን አሰራር መሰረት ጥምረት 3ኛው ደረጃ ሲሆን ከአባል ሕብረቶች ሁለት ሁለት ተወካዮች በጥንቃቄ ተመርጠው ጥምረቱ ይመሰርታሉ፡፡ በመጀመሪያ ከ 8 እስከ 10 የሚሆኑ ሕብረቶች ጥምረቱን ይመሰርታሉ፤ ከዚያም የአባል ጥምረቶች ቁርጥ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የራስ አገዝ ጥምረት የራሱን ራዕይ፤ ተልኮ እና ግብ ሁሉንም በራስ አገዝ የተደራጁ አባላትን በማሳተፍ በማውጣት፤ ለትግበራው ይንቀሳቀሳል፡፡
በራስ አገዝ አሰራር መሰረት ጥምረት አራት ዋና ዋና የስራ ሚናዎች ይኖሩታል፡፡ እነርሱም፤
1ኛ. ጠንካራ የህዝብ ተቋም መመስረት እና ማስቀጠል
2ኛ. የህብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ማመቻቸት
3ኛ. ለማህበረሰብ ሰላም፤ ደህንነት እና ፍትህ መስራት
4ኛ. በመንግስት ፓሊሲና በህብረተሰቡ አስተሳሰብ ላይ በጎ ተፅዕኖዎችን ማሳደር

+ የእድገት ባንድነት ጥምረት አመሰራረት

እድገት ባንድነት ጥምረት በአማራ ክልል ደብረማርቆስ ከተማ በ 8 ህብረቶች እና 67 የራስ አገዝ ቡድኖች የተደራጁ 1088 አባላትን በማካተት ከጥር 2002 ዓ.ም ጀምሮ እየተንቀሳቀሱ ይገኛል፡፡        

የቁጥር መረጃዎች ፡-     የአባል ቡድኖች ብዛት 67
የሕብረቶች ብዛት 8
ጠቅላላ አባላት ብዛት 1088
አጠቃላይ የቡድኖች ቁጠባ 576 ሺ 444 ብር
አጠቃላይ አባላት የተሸከረከረ ብድር 1 ሚሊዩን 104 ሺ 940 ብር
የእድገት ባንድነት ራዕይ

  • ሠላም፤ ፍትህ ፤ እኩልነት የሰፈነባት እና ከድህነት የተላቀቀች ኢትዮጵን ማየት፡፡

ተልዕኮ

  • የማህበረሰቡ እኩልነት መከበሩን ማረጋገጥ፡፡

ግብ

  • የራስ አገዝ ቡድኖች በሰፊው ማደራጀት፡፡

+ በጥምረቱ የሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች


1ኛ. ጥምረቱን ለተለያዩ አካላት የማስታወቂያ ፕሮግራሞችን ማድረግ፤
2ኛ. የጥምረቱን ራዕይ፤ ተልዕኮ እና ግብ አባል የራስ አገዝ ቡድኖችና ህብረቶች የማሳተፍ ማውጣት፤
3ኛ. የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ለልጆቻችን እንሮጣለን በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ አዘጋጅተናል፡፡
4ኛ. በአባል ህብረቶች መካከል የልምድ ልውውጥ እና ራስ በራስ መማከር መድረክ ማዘጋጀት፤
5ኛ. አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት በየአመቱ ታላላቅ ኩነቶችን ማዘጋጀት፤
6ኛ. አባል ቡድኖችን እና ህብረቶችን በማነቃቃት የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን፤ ችግኝ ተከላ ወዘተ ስራዎችን መስራት፤
7ኛ. ህብረተሰቡን በማሳተፍ የመተላለፊያ ድልድይ ተሰርቷል፤
8ኛ. የልጅ ማጥባት ቀንን ምክንያት በማድረግ የግንዛቤ ስራዎች ተሰርቷል፤
9ኛ. ከቤተሰብ መምሪያ ጋር በመተባበር በኤች አይ ቪ ምክርና ምርመራ፤ የቤተሰብ ምጣኔ ስልጠናዎችን ለህብረቶች ማመቻቸት፤
10ኛ. ከደብረ ማርቆስ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ጋር ብዙ ስራዎችን መስራት በመቻሉ የከተማው ከንቲባ የእውቅና ደብዳቤ ሰጥተዋል፤
11ኛ. ለራስ አገዝ ቡድን አባላት ሴቶች የቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አመቻችቷል፤
12ኛ. ከከተማው ፖሊስ፤ ፍትህ አካላት ጋር በመተባበር ጫት፤ ሺሻ እንዲሁም የምሽት ጭፍራ ቤቶችን ማዘጋት
13ኛ. የተለያዩ ስልጠናዎችን ለቡድን እና ህብረት ተወካዮች በጊዜው ማመቻቸት፤
14ኛ. ከአጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ ገዜው የሚጠይቀውን ስራዎችን መስራት፤
15ኛ. የኮሳፕ አመታዊ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባዎች ላይ በቋሚነት ይሳተፋል፡፡