Consortium of Self Help Group Approach Promoters (CoSAP) is an umbrella of SHG promoting organizations. Members, who adopt the SHG approach as a key tool for the empowerment of women, utilize this platform as a unifying mechanism for the implementation of the approach. This objective is realized through the provision of capacity building training to member organization and representing them in any policy level discussion that paves the ground for the proliferation of the approach.

+251-115-525251
info@shgconsortiumeth.org
Lideta Sub City, Woreda 10, African Union Area
+251-115-525251

መግቢያ

የራስ አገዝ ጥምረት በራስ አገዝ ቡድን አሰራር መሰረት 3ኛው እና የአሰራሩ መገለጫ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በስራ ላይ ከሚገኙት ጥምረቶች መካከል በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ላይ የሚንቀሳቀሰው አንለይ ጥምረት አንዱ ነው፡፡ ይህ አንለይ ጥምረት ድረ ገፅ ስለ ጥምረቱ አመሰራረት እና እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቅ ነው፡፡ ስለ አንለይ ጥምረት የበለጠ ለማወቅ ከታች ያሁትን መረጃዎች እንዲገቡ በክብር እንጋብዛለን፡፡
አብራችሁን ለመስራት በአድራሻችን አግኙን፡፡    

+ ስለ ራስ አገዝ ጥምረት ፅንሰ ሀሳብ

በራስ አገዝ ቡድን አሰራር መሰረት ጥምረት 3ኛው ደረጃ ሲሆን ከአባል ሕብረቶች ሁለት ሁለት ተወካዮች በጥንቃቄ ተመርጠው ጥምረቱ ይመሰርታሉ፡፡ በመጀመሪያ ከ 8 እስከ 10 የሚሆኑ ሕብረቶች ጥምረቱን ይመሰርታሉ፤ ከዚያም የአባል ጥምረቶች ቁርጥ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የራስ አገዝ ጥምረት የራሱን ራዕይ፤ ተልኮ እና ግብ ሁሉንም በራስ አገዝ የተደራጁ አባላትን በማሳተፍ በማውጣት፤ ለትግበራው ይንቀሳቀሳል፡፡
በራስ አገዝ አሰራር መሰረት ጥምረት አራት ዋና ዋና የስራ ሚናዎች ይኖሩታል፡፡ እነርሱም፤
1ኛ. ጠንካራ የህዝብ ተቋም መመስረት እና ማስቀጠል
2ኛ. የህብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ማመቻቸት
3ኛ. ለማህበረሰብ ሰላም፤ ደህንነት እና ፍትህ መስራት
4ኛ. በመንግስት ፓሊሲና በህብረተሰቡ አስተሳሰብ ላይ በጎ ተፅዕኖዎችን ማሳደር

+ የአንለይ ጥምረት አመሰራረት

አንለይ ጥምረት በጅማ ከተማ በ 15 ህብረቶች እና 122 የራስ አገዝ ቡድኖቸ የተደራጁ 1772 አባላትን በማካተት የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡
የጥምረቱ አባል ቡድኖች እና ህብረቶች በተለያየ ምክንያት መቀነስ አሳይቶ በአሁኑ ጊዜ በ57 ቡደኖች እና 10 ህብረቶችን የተደራጁ 1652 አባላትን ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡         

የቁጥር መረጃዎች ፡-     የአባል ቡድኖች ብዛት 57
የሕብረቶች ብዛት 10
ጠቅላላ አባላት ብዛት 1652
አጠቃላይ የቡድኖች ቁጠባ 938 ሺ 872 ብር
አጠቃላይ የቡድኖች ካፒታል 1 ሚሊዩን 752 ሺ 650 ብር

የአንለይ ጥምረት ራዕይ

  • ከድህነት የተቀላቀለች፤ ሰsላምና ፍትህ የሰፈነባት እና እናቶች የተሻለ ሕይወት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ማየት

ተልዕኮ

  • የራስ አገዝ ቡድኖች እና ህብረቶች ራዕይ መሳካት እገዛ ማድረግ
  • በጅማ ከተማ እናቶች እንዲደራጁ ድጋፍ ማድረግ
  • በከተማችን ውስጥ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች አስተዋጽኦ ማበርከት፡፡

ግብ  

  • እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ 5000 እናቶችን በራስ አገዝ ቡድን ተደራጅተው ከድህነት ተላቀው ማየት፡፡

+ በጥምረቱ የሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች


1ኛ. በስሩ ላሉ የራስ አገዝ ቡድኖችና ህብረቶች የማጠናከር እ ና ክትትል ድጋፍ መስጠት፤
2ኛ. ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ክብረ በዓልን በጅማ ከተማ ሴቶችና ህጻናት እንዲሁም ከተለያ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተለያ ዝግጅቶች ያከብራል፤
3ኛ. በህፃናትና ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እንዲቆሙ ከፍትህ አካላት ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በየጊዜው የይሰራል፤
4ኛ. ኤች አይ ቪ፤ የልጆች ጉልበት ብዝበዛ፤ የሴቶችና ህፃናት መብት ጥሰት ወዘተ ዉሪያ የተለያዩ የንቅናቄ እና ዘመጫዎችን ማካሄድ፤
5ኛ. የጅማ ከተማ አስተዳደር በሰጠዉ የመሬት ድጋፍ ለቡድኖች እና ህብረቶች ቢሮዎች እና ቋሚ የገቢ ማስገኛ እንዲኖራችው ማስቻል፤
6ኛ. ከተለያ አካላት ጋር በመተባበር በጅማ ከተማ የአፈር እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ በንቃት መሳተፍ፤
7ኛ. በጅማ ከተማ አስተዳደር ከሄርማታ ቀበሌ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ፈጽሟል፤
8ኛ. የተለያዩ ስልጠናዎችን ለቡድን እና ህብረት ተወካዮች ያመቻቻል፤
9ኛ. ከአጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ ጊዜው የሚጠይቀውን ስራዎችን ይሰራል፤   
10ኛ. የኮሳፕ አመታዊ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባዎች ላይ በቋሚነት ይሳተፋል፡፡

+ የአንለይ ጥምረት መዋቅር

+ የጥምረቱ አድራሻ

አንለይ ጥምረት
ጅማ ከተማ፤ ሔርማታ ቀበሌ
ስልክ ቁጥር 0471118517
ፖ.ሳ.ቁ 760
ኢ-ሜይል፡
ጅማ፤ ኢትዮጵያ